ስለ ኢትዮጵያ ስሞች

 • ኢትዮጵያ የተጠራችባቸውና የተጠቀሰችባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፥ በከፊል:- [በቅድሚያ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ትርጉም፥ “ጦቢያ፣ ጹብያ፣ ጹብ ያሕ፣ የሕያው ቅዱስ፣ ምድራዊ ገነት፣ መንፈሳዊ ዓለም... ማለት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።]
  1. ምድያም ~ Midian- ሙሴ ከግብጽ ሸሽቶ ለ40 ዓመታት የኖረበት አገር። “...ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ በውኃም ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።” (ዘጸ 2:15) ፥ “የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።” (ዕን 3: 7) ፥ “ሙሴም ከዚህ ነገር የተነሣ ሸሽቶ በምድያም አገር መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ሁለት ልጆች ወለደ።” (ሐዋ 7:29)
  [ምድያም ~ Madian, Midian, Midianites: መዳኛ፣ ፍርድ የሚሰጥበት፣ ፍትኅ የሚታይበት፣ መናገሻ፣ ፍትኅ የሰፈነበት፣ ዋና ከተማ፣ የምድያም አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማዴ፣ ማዶ፣ ሜዳን፣ ምድያዊ...]
   ምድያም / Madian: ሙሴ በግብፅ ከፈርዖን ፊት ሸሽቶ ለአርባ ዓመት የኖረበት አገር፥ (ሥራ 7:29)
   ምድያም / Midian: የአብርሃም ልጅ፥ ከኬጡራ የወለደው። (ዘፍ 25:2)
  • ምድያም / Midianites:
  “የምድያም ነጋዶችም አለፉ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት ...” (ዘፍ 37:28፣ 36)
  • ሙሴ በግብፅ ከፈርኦን ፊት ሸሽቶ የሄደበት፥ “ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ በውኃም ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።” (ዘጸ 2:15-21) ፣ “ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ወደደ ልጁንም ሲፓራን ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።” (ዘጸ 2:21)]
  2. ሳባ ~ Sheba- ሰሎሞንን ለመስማት ወደ ኢየሩሳሌም የሄደች፥ ኢትዮጵያዊት፥ “የሳባም ንግሥት በእግዚአብሔር ስም የወጣለትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።” (1 ነገ 10: 1)
  [ሳባ ~ Seba, Sheba: ሰባ፣ ሰብዓ፣ ሰብ፣ ሰው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት...]
  ‘ሰብዓ’ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
  I. ሳባ / Seba:
  1. የኩሽ ልጅ ሳባ፥ “የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ ...” (ዘፍ 10:7)
  2. ሳባውያን፥ (ኢሳ 43:3)
  II. ሳባ / Sheba:
  1. የራዕማ ልጅ፥ “... የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው” (ዘፍ 10:7)
  2. የዮቅጣ ልጅ፥ (ዘፍ 10:28፣29)
  3. የአብርሃም ልጅ፥ የዮቅሳን ልጅ፥ “ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። ...” (ዘፍ 25:3)
  4. “እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል...” (ኢሳ 45:14)
  5. “… የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።” (መዝ 72:10)
  • የብንያማዊ የቢክሪ ልጅ፥ ሳቤዔ - (2 ሳሙ 20:1)
  • ሤባ- (ኢያ 19:2)
  3. አዜብ ~ south- አብርሃም ከግብጽ ወጥቶ የሔደበትና የኖረበት አገር፥ “አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ።” (ዘፍ 12:9) ፥ “ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ፤ በአዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና።” (ዘፍ 24:62) ፥ “ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።” (ማቴ 12:42)
  4. ኢትዮጵያ~ Ethiopia- ኢትዮጵያ የግዮን ወንዝ መገኛ፥ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” (ዘፍ 2፡13)፥ “ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።” (ዘኁ 12:1)
  [ኢትዮጵያ ~ Ethiopia, Cushan: ኢትዮጵያ፣ ጦቢያ፣ ጹብያ፣ ጹብ ያሕ፣ የሕያው ቅዱስ፣ ምድራዊ ገነት፣ መንፈሳዊ ዓለም... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- ኩሽ፣ ሳባ፣ አዜብ፣ ኬጢ፣ ምድያም፣ የአለም ዳርቻ]
  • ኢትዮጵያ / Ethiopia: ኢትዮጵያ የግዮን ወንዝ መገኛ፥ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” (ዘፍ 2፡13)
  • ኢትዮጵያ / Cushan: የአብርሃም ልጅ፥ የምድያም አገር፣ “የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ” (እንባ 3፡7)
  ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ~ Ethiopian eunuch, the: እጩ መኮንን፣ አልጋ ወራሽ ማለት... ነው። የኢትዮጵያ ባለስልጣን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር... ማለት ነው።
  የንግስት ህንደኬ አዛዥና ጃንደረባ፣ ኢትዮጵያዊው፥ “ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር” (ሐዋ 8፡ 27)
  ኢትዮጵያዊት ~ Ethiopian woman: ጦቢያዊት፣ ጹባዊት፣ ኢትዮጵያዊት፣ ሳባዊት፣ ምድያማዊት... ማለት ነው።
  የነቢዩ ሙሴ ሚስት፥ ሲፖራ፥ “ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ...” (ዘኁ 12፡1)
  5. ኩሽ ~ cush- የሳባ አባት፥ በሳባ ሳባውያን፥ በኩሽ ኩሻውያን ይላሉ፥ “የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።” (ዘፍ 10:8)
  [ኩሽ ~ Cush: ኩሺ፣ ካሺ፣ ካሽ፣ ካሳ የሚክስ፣ ኩሻዊ፣ ኢትዮጵያዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኩሲ፣ ኵሲ]
  Cush- ‘ካሽ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
  ከሦስቱ የኖኅ ልጆች፣ የካም ልጅ፥ “የካምም ልጆች ኩሽ...” (ዘፍ 10:6)፣ “ኩሽም ናምሩድን ወለደ ...” (ዘፍ 10፡8)]
  6.ኬጢ ~ Heth- አብርሃም ከግብጽ ወጥቶ የኖረበት አገር፥ ኢትዮጵያ፥ “አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ ለኬጢ ልጆች፥ ሰገደ።” (ዘፍ 23:7) ፥ “ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፦ ይህች የኤልያብ ልጅ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን? አለ።” (2 ሳሙ 11:3) ፥ “አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ። እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት።” (ዘፍ25:1ና2)
  [ኬጢ ~ Heth: ‘ቀጢ፣ መንቀጥቀት፣ መውረግረግ’ ማለት ነው። የከንዓን ልጅ፥ የኬጢያውያን አባት፥ “ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥” (ዘፍ 10:15)
  ኬጢያውያን ~ Hittites: ሄታይት፣ የኬጢ ወገኖች፣ የኬጢ አገር ሰዎች ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም- ቄኔዛዊው]
  የከነዓን ልጅ፥ “ቀድሞናውያንንም ኬጢያውያንንም” (ዘፍ 15:19)]
  7. የምድር ዳር ~ the uttermost parts of the earth- ጌታ በትምህርቱ የጠቀሳት አገር፥ የኢትዮጵያ ንግሥት፥ ንግሥተ ሳባ፥ “ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።” (12:42) 

ይቀጥላል